በደ/ም/ኢ/ክልል የምዕራብ ዞኖች አካባቢ ትራንስፖርት ማህበራት የጋራ የምክክር ፎረም በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ተካሂዷል።
በወቅቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሸካ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀራ እንደተናገሩት በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ነው ብለዋል።
መንግስት በሚያወጣው የትራንስፖርት አዋጅ፣ደንብና መመሪያ መሠረት የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰፍኖ ማየት የፎረሙ ግብ እንደሆነም አንስተዋል መምህር ዘላለም።
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም በርካታ የስምሪት መንገዶች የተበላሹና ጥገና የማይደረግላቸው በመሆኑ በባለንብረቱ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማስከተሉ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን መፍትሄ ይፈልጋልም ተብሏል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ የተደረገው የዲጂታል ኢ-ትኬቲንግ አገልግሎት በክልሉ በሚገኙ መናኸሪያዎች ላይ ወጥ በሆኑ መልኩ ያለመቀጠሉና አገልግሎት አሰጣጡም ቢሆን በተፈለገው ደረጃ ያለመሆኑ አንዱ ማነቆ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በመድረኩ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሸካና የቤንች ሸኮ ዞን፣ከኦሮሚያ ክልል የጅማ እና ኢሉአባቦራ ዞን እንዲሁም ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።