ማሻ፣ ጥር 6፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ)”ቢስት ባር “የመደመር እሳቤ በተግባር የሚገለጽበት በዓል ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)ተናገሩ፡፡
የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” ማጠቃለያ መርሐ ግብር በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል።
በበዓሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋነሽ ኬሌሮ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች፣ የቤንች ብሔር የጎሳ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ታድመዋል።
ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ በቢስት ባር በዓል የብሔሩ አባላት ተሰብስበው በአብሮነት የሚያሳልፉትና መጪውን አዲስ የመደመር አስተሳሰብ በተጨባጭ የሚገለጽበት ነው ብለዋል።
ይህ ድንቅ ባህል ተጠንቶና ተሰንዶ ለትውልዱ ሊተላለፍ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ የብሔሩ ምሁራን ማህበረሰቡ ያዳበረውን ቱባ የባህል እሴት ለሰላምና ለዕድገት እንዲውል በማድረግ ሁሉም የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን÷ የለውጡ መንግስት ለባህል በሰጠው ትኩረት በርካታ ቱሪስቶች አካባቢው እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቢስት ባር ለበኩር ቅድሚያ የሚሰጥበት፣ መተሳሰብ ፣ መደማመጥ ያለበት ድንቅ በዓል ነው ያሉት አስተዳዳሪው ይህንን በዓል ለቀጣይ ትውልድ ጠብቆ የማቆየት ሃላፊነት አለብን ነው ያሉት፡፡
(ኤፍ ኤም ሲ)
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …