ማሻ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ደቡብ ኮሪያ ዛሬ ሌሊት ላይ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የሰባት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አወጀች።
181 ሰዎችን ከታይላንድ ባንኮክ አሳፍሮ ደቡብ ኮሪያ የደረሰው አውሮፕላን ሙአን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሶ 179 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
ሁለት የአውሮፕላኑ ሰራተኞች በህይወት ተርፈው ወደ ህክምና ተቋም እንዲገቡ መደረጉን የሀገሪቱ መንግስት ገልጿል።
በአደጋው የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ በታወጀው ሰባት ብሔራዊ የሐዘን ቀናት በሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብና የመንግስት ሰራተኞችም ጥቁር ሪባን እንዲያስሩ ትዕዛዝ ተላልፏል።
ጀጁ የተባለ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር ከአውሮፕላን ማረፊያ አጥር ጋር ተጋጭቶ አደጋው መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።
ምንጭ ከኤፍ ኤም ሲ ነው
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አደጋውን አስመልክተው ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን ለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተትም ኃላፊነት እወስዳለሁ ብለዋል።
የአውሮፕላኑ የበረራ መረጃ መመዝገቢያ ሳጥን (ብላክ ቦክስ) የተገኘ ሲሆን የአደጋውን መንስኤ መርምሮ ለማወቅ ጊዜ ይወስዳል ተብሏል።
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።