እስካሁን 499 ሺህ 200 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በአገልግሎቱ የተፈታኞች ምዝገባ፣የፈተና ዕርማትና ውጤት ጥንቅር ዴስክ ሀላፊ ማዕረፉ ሌሬቦ÷በ2017 የትምህርት ዘመን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመደበኛና በግል 750 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የመደበኛ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን÷ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ሃላፊው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
የኢንተርኔት አማራጭ በሌለባቸው አካባቢዎች ተማሪዎች ከኢንተርኔት ውጭ ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሰራበት አካባቢ ሄደው መረጃቸውን ወደ ኦንላይን መጫን እንደሚችሉ ተናግረዋል።
በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በመግለጽ እስካሁን ድረስም 82 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች ለፈተናው ምዝገባ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረው እስካሁን ድረስ 1 ሺህ 100 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አመላክተዋል።
ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎች እንደማይስተናገዱ እና ፈተና ላይ እንደማይቀመጡ ተጠቁሟል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል
More Stories
በቀጣይ 90 ቀናት የተቀመጡ ዕቅዶችን በውጤታማነት በመፈጸም እመርታዊ ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል፦አቶ ፍቅሬ አማን
ምክር ቤቶች የህዝቡ ሁለተናዊ ተጠቃሚነት እንድረጋጥ ድርሻቸው የጎላ በመሆኑ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ማጠናከር እንደምያስፈልግ ተጠቆመ ።
ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ እያከናወነች ያለው ተግባር የሚደነቅ ነው