በኦሚኒ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አስተባባሪት እንደ ሀገር በስድስት ክላስተር ጣቢያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የኦሚኒ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስራአስኪያጅ ቤኛ ስሜሶ እንደተናገሩት እንደ ሀገር ያሉ የማህበረሰብ ሚዲያ ተቋማትን በ ስድስት የክላስተር ጣቢያዎች በአርባ ምንጭ፣በጂማ፣በሐዋሳ፣ በባህር ዳር፣በድረዳዋና በአዲስአበባ ክላስተር ጣቢያዎች በዶቸበሌ አካዳሚ ከGIZ ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ስልጠና መስጠቱን ተናግሯል።
የመጀመሪያው ዙር የሚድያ ባለሙያዎችና ስራአስኪያጆች ስልጠና በአርባምንጭ ከተማ የተሰጠ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ደግሞ ከካፋ ፣ ከሸካ ፣ከጋምቤላ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች እንዲሁም ከጅማ ፣ከመቱእና ከደምቢዶሎ ዩንቨርሲቲዎች ለመጡ የማህበረሰብ ሚድያ ባለሙያዎችና አመራሮች በጅማ ከተማ እየተሰጠ እንደሚገኝና በሌሎች የክላስተር ማዕከላትም እንደሚቀጥል አክለዋል።
በአስተዳደር ህግ ፣ በማህበረሰብ ሬድዮ ፕሮግራሞችና ዜናዎች ዝግጅት፣ የማህበረሰብ ሚዲያ ተቋማት ቀጣይነት ያለውና እያደገ የሚሄድ ገቢ በማመንጨት በሰው ሃይልና በሚድያ መሳሪያዎች አቅማቸውን በማሳደግ ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ና በለሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም ነው ስራ አስኪያጅየገለፁት።
በተቋማት አካባቢ የሚፈጠሩ የአስተዳደራዊ ችግሮች እንዲፈቱ ወደ መደበኛ ፍርድቤቶች ከመሄድ ይልቅ በአስተዳደራዊ ህግ መፍታት የተሻለ አማራጭ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ከሚዲያ ተቋማት እንደሚጠበቅም በስልጠናው ላይ ተሰቷል ።
ሰልጣኞች በበኩላቸው ከስልጠናው ቀጣይ ስራቸውን ለመስራት የሚያስችል ግንዛቤ እንዳገኙ ገልፀው በተለይም በአስተዳደራዊ ህግ ዙርያ ያሉባቸውን ክፍተቶች መሙላት እንዳስቻላቸው አክለዋል።
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ