የሀማስ ጊዜያዊ መሪ ካሊድ ማሻልን ጨምሮ ሌሎች የቡድኑ የፖለቲካ ቢሮ አመራሮች በኳታር ይኖራሉኳታር በሀገሪቱ የሚኖሩ ከፍተኛ የሀማስ አመራሮችን ለማስወጣት ከአሜሪካ የቀረበላትን ጥያቄ መቀበሏ ተሰማ፡፡ሀማስ በ2012 በሶርያ የእርስ በእርስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ዋና ቢሮውን ከደማስቆ ወደ ዶሃ አዘዋውሯል፡፡የጥቅምት ሰባቱን ጥቃት ተከትሎ አሜሪካ “ኳታር በተለመደው መንገድ ከቡድኑ ጋር ግንኙነቷን መቀጠል እንደማትችል” ስታስጠነቅቅ ሰንብታለች፡፡ ሀገሪቱ በዶሃ የሚገኘውን የቡድኑን ዋና ቢሮ እንድትዘጋ እና ለሀላፊዎቹ ጥገኝነት ከመስጠት እንድትቆጠብ ጫና ስታደርግ መቆየቷን ሲኤንኤን የአሜሪካ እና ኳታር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ዘገባው ሀማስ ታጋቾችን ለመልቀቅ እና የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ የቀረበለትን ተደጋጋሚ ጥያቅ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ፤ መሪዎቹ በማንኛውም የአሜሪካ አጋር ዋና ከተሞች ተቀባይነት ሊያገኙ አይገባም የሚል ሀሳብ በዋሽንግተን በኩል መንጸባረቁን ጠቅሷል፡፡
al-ain
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ