6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ነገ ይካሄዳል። በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1 ዓመት ስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ አስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ ድንጋጌ መሰረት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በተገኙበት ነገ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ለሁለቱ የፌደራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ስራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
EBC
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ