ያለፉት ሁለት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን ማሳየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አካል የሆነውንና በቅርብ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አፈፃፀም ገምግመናል ብለዋል።ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት መቻሉንም ገልጸዋል፡፡በተመሳሳይም የገቢ ግባችንም የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።በአጠቃላይም ያለፉት ሁለት ወራት ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል ሲሉም ነው የገለጹት።
FBC
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ