በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስል ጄነራል ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ÷ በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ከሊባኖስ መውጣት የሚችሉበትን መንገድ እያመቻቸ መሆኑን አስታውቋል፡፡በዚሁ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የሚፈልጉ እና እስከ አሁን ያልተመዘገቡ ወገኖች አስፈላጊውን መረጃ በማዘጋጀት እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ለምዝገባ አስፈላጊ የሆኑት መረጃዎችም÷ ሙሉ ስም ከነአያት(ፓስፓርት ላይ እንደተፃፈው)፣ የፓስፖርት ቁጥር፣ በሊባኖስ የቆይታ ጊዜ፣ የሊባኖስ ስልክ ቁጥር መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡ለምዝገባ የተዘጋጁት ስልክ ቁጥሮችም÷ 03-29-89-78፣ 76-03-08-23፣ 81-99-46-34፣ 70-29-80-91፣ 81-80-25-18፣ 70-84-25-24 እና 81-09-27-46 መሆናቸውን የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡ጽሕፈት ቤቱ ቀደም ሲያል ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተመዘገቡና መመዝገባቸውን ያረጋገጡ ወገኖች በድጋሚ እንዳይመዘገቡ አሳስቧል፡፡
በሊባኖስ በተከሰተው ውጥረት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ምዝገባ እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀረበ፡፡

More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ