የሽኝት መርሐ-ግብሩ ሲጠናቀቅም የቀብር ስርዓቱ በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ዛሬ 8 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።ፕሮፈሰሩ በገጠማቸው የልብ ህመም በሀገር ውስጥ እና በኬኒያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡በኢንስቲትዩቱ ለተመራማሪዎች የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና በማመቻቸት ሙያቸውን እንዲያሳድጉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ሲሆን፥ ጀማሪ ተመራማሪዎችም አቅማቸውን አጎልብተው ትርጉም ያለው የምርምር ስራ እንዲሰሩ ጥረት ማድረጋቸው ይነገራል፡፡ሁሉም የምርምር ስራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ከማስቻል ባለፈ የምርምር ውጤቶች ለህብረተሰቡ እንዲደርሱና የሚመለከተው አካልም እንዲጠቀምባቸው በማድረግ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የአስክሬን ሽኝት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …