ድጋፉን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፋት የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ወንድሙ ግርማ ይህ ዓይነቱ ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረዉ ይሰራል ብለዋል።በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦችንና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር 350 ለሚሆኑ ለተቸገሩ ወገኖች አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለእያንዳዳቸዉ የ 2 ሊትር ዘይትና የ4 ኪሎ ግራም ዱቄት ድጋፍ መበርከቱን የተናገሩት ደግሞ በቴፒ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሴቶች ሊግ ሀላፊ ወይዘሮ ይጋርዱ ጤናዉ ናቸዉ። በተመሳሳይ በከተማዉ መዋቅር ዉስጥ የሚሰሩና ከ2 ሺህ ብር በታች የሚከፈላቸዉ 126 ደመወዝተኞችም ለእያንዳንዳቸዉ የ5 ሊትር ዘይት ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል። ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ።
አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ 350 ለሚሆኑ በቴፒ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ መበርከቱ ተገለጸ።
More Stories
የአየር ጠባይ ትንበያ መረጃ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት በታቀደው መሠረት እንዲከናወን ድርሻውን ተውጥቷል – ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)
መጪው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ተባለ።
የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት በማለም ለተጀመረው ርብርብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ።