ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ተቋቁማ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች መሆኗን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር መሆኗንም አንስተዋል፡፡ ሀገሪቱ ያላት የካፒታል ገበያ፣ የተወሰዱ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና ሌሎች ሁኔታዎች፤ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንደሚያደርጓትም ጠቁመዋል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚን በመገንባት ሂደት ላይ መሆኗን መናገራቸውን ፋና ዘግቧል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፤ በጤናው ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችሉ መሰረተ-ልማቶች የተሟሉ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡የኢትዮ-ቻይና ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በቻይና ቤጂንግ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
EBC
More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ