የቴፒ ከተማ ምክር ቤት አያካሄደ ባለዉ 2ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤዉ የከተማውን የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምንና የ2017 ዕቅድና የማስፈፀሚያ በጀት ቀርቦ ተወያይቶ አፅድቋል።
የቴፒ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተካልኝ ሻወኖ የፍርድ ቤቱን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምንና የ2017 ዕቅድና የማስፈፀሚያ በጀት ለጉባኤዉ አቅርበዉ በአባላቱ ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበታል።
በዚህም በ2016 በጀት ዓመት በጥቅል 1 ሺህ 1 መቶ 97 መዝገቦች ቀርበው በፍትሀብሔርና በወንጀል 1 ሺህ 1 መቶ 84ቱ ላይ ውሳኔ መስጠት መቻሉን ተናግረዉ ቀሪዉ 13 መዝገቦች በቀጣይ እንዲታዪ መዘዋወራቸዉን አንስተዋል።
በተያያዘም በ 2017 ዕቅድ ማስፈፀሚያ በጀት ከ 9 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ሆኖ ቀርቦ በምክር ቤቱ ሙሉ ድምፅ ቀርቦ ፀድቋል።
ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ