የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት እና ሰላም ከማረጋገጥ ባለፈ በልማቱ ላይ እያደረገ ያለው ተሳትፎ አበረታች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር ) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንደገለጹት ÷መከላከያ ሠራዊት የሰላም ምንጭ ብቻ ሳይሆን የልማት እና የፈጠራ ምንጭ መሆን ስላለበት በዚህ አግባብ እየተመራ እየተገኘ ያለው ውጤት ተስፋ ሰጭ ነው ፡፡ይህም ተስፋ ሰጭ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ነው ያሉት ።በስንዴ ምርት በእርሻ በ #አረንጓዴዓሻራ ብዙ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በማምረት ልማቱን ለማሳለጥ እና የብልፅግና መሰረት ለመጣል እያደረገ ያለው ጥረት ሊበረታታ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
FBC
More Stories
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል
በክልሉ ተደራሽነቱና ፍትሃዊቱ የተረጋገጠ የፍትሕ እና የዳኝነት ሥርዓት እንዲሰፊን የተጀመረው የትራንስፎርሜሽን ሥራዎች መጠናከር አለባቸዉ፦ክብርት ወ/ሮ ሃና አረአያስላሴ