በግብርናው ዘርፍ በተደረገው ሪፎርም የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ ሥራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።አቶ ተመስገን “የግብርናውን ዘርፍ እምቅ አቅም እንጠቀም” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ መካሄድ የጀመረውን ሀገር አቀፍ የግብርና ኢንቨስትመንት ፎረም ከፍተዋል፡፡በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ ለግብርና ሥራ ተስማሚ አየርና ከባቢ እንዳላት ገልጸው÷ የግብርናውን ዘርፍ በልዩ ትኩረትና ዘመናዊ አሠራር ደግፎ ውጤት ለማምጣት መንግሥት እና አርሶ አደሩ በቁርጠኝነት እየሠሩ ነው ብለዋል፡፡በዘርፉ ፈጣንና ቀላል አሠራሮችን በዘመነ መንገድ ለማከናወን የተጀመሩ ውጤታማ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው÷ የውጭ ኢንቨስተሮችም ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ በተገበረችው ሪፎረም ከራሷ አልፎ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ መጀመሯን አንስተው÷ ውጤቱም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እያበረታታ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡የምግብ ሉዓላዊነት ላይ የሚተገበሩ ተነሳሽነቶችና ፕሮጀክቶች ሳይቆራረጡ ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው ያመላከቱት ደግሞ የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና የኢኮኖሚ አማካሪ ማክሲሞ ቶሬሮ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያሳየች ያለውን ውጤት አድንቀው÷ ድርጅታቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የግብርናና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
FBC
More Stories
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።
የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር ሁለተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገለፁ።
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል