የገቢዎች ሚኒስቴር ከመካከለኛ ግብር ከፋዮች ጋር በታክስ ህግ ተገዥነት እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፤ የመንግስት ዋነኛ ትኩረት ከግብር የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ መሆኑን ተናግረዋል። የገቢ አሰባሰቡ ህግና ስርዓትን የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል በመንግስት የሚመራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል። የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ ተቋማት በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል። የገቢዎች ሚኒስትሯ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው፤ የገቢ አሰባሰቡን ለማሳደግ በቀጣይ ዓመታት 5 ዋና ዋና ስትራቴጂክ እቅዶች ተነድፈው እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት የመንግስት ዋነኛ ትኩረት ገቢን ማሳደግ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ተናገሩ።
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …