በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡በዚሁ መሠረት ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በሚካሄደው 3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ ይሳተፋሉ፡፡እንዲሁም ቀን 6 ሠዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው 5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ቢንያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ተሳታፊ ናቸው፡፡በሌላ በኩል እንዲሁም ትናንት በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ከምድቧ ያላለፈችው አትሌት ብርቄ ሓየሎም ዛሬ ቀን 7 ከ45 ላይ በድጋሚ በማጣሪያው የምትወዳደር ይሆናል፡፡በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምክ ኢትዮጵያ እስከ አሁን ሁለት የብር ሜዳሊዎችን በመያዝ 52ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡አሜሪካ፣ ቻይና፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይ በቅደም ተከተል ከ 1 እስከ 4 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
FBC
More Stories
የሸካ ዞን የታዳጊ ወጣቶች የእግርኳስ ቡድን የ2018 ክልል አቀፍ ውድድር የዋንጫ አሸናፊ ሆነ።
5ተኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የባህል ስፖርቶች ውድድር፣ የባህል ፌስቲቫል እና የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር የታለመውን ግብ ያሳካ መሆኑ ተገለጸ።
ባካሪ ሳኛ ኢትዮጵያ ገባ