አንድነት እና አብሮነትን የሚጎዱ የጥላቻ፣የተዛቡና ሌሎች ትርክቶችን መከላከልና ኢትዮጵያዊነትን የሚገነቡ ትርክቶችን ማጉላት ይገባል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡
የ26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን በዓል አካል የሆነው የአብሮነት ቀን ዛሬ ተከብሯል።
በክብረ በዓሉ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ÷ “ኢትዮጵያውያን በታሪክ ከመቆራኘት ባለፈ የጋራ እሴት፣ ባህል፣ አኗኗር እና ወግ ያለን ህዝቦች ነን”
ትውልዱ መገለጫችን የሆነውን የአብሮነት ባህል አበልጽጎ ለመጪው ትውልድ ሳይሸራረፍ ማስረጽ እንደሚጠበቅበትም አመልክተዋል።
አንድነት እና አብሮነትን የሚጎዱ የጥላቻ፣ የተዛቡና ሌሎች ትርክቶችን መከላከልና ኢትዮጵያዊነትን የሚገነቡ ትርክቶችን ማጉላት ይገባልም ብለዋል።
በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው ልማት ፍትሃዊ፣ ሁሉንም ያማከለና ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ኦርዲን ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ