ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት የማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒ ካፑአኖ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው÷ በማደግ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ የጉዞ እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ላይ መክረዋል።
በባህል ሀብቷ እና ታሪካዊ ቅርስ ይዞታዋ ብሎም በአስደናቂ የመልክዓ ምድር ገፅታዋ የታወቀችው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋን በማስፋፋት ላይ አተኩራለች መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዓለም ዙሪያ 8 ሺህ 785 ያህል ቅርንጫፎች እና የሀብት አድራሻዎች በመያዝ በመስተንግዶ እና ማረፊያ አገልግሎት ዘርፍ መሪ የሆነው ማሪዮት ኢንተርናሽናል በዚህ ስራ ጉልህ ሚና ለመጫወት ትልም ይዟል ተብሏል።
More Stories
የአየር ጠባይ ትንበያ መረጃ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት በታቀደው መሠረት እንዲከናወን ድርሻውን ተውጥቷል – ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)
መጪው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ተባለ።
የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት በማለም ለተጀመረው ርብርብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ።