የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በጣሊያን ሴኔት የውጭ ጉዳይና መከላከያ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሴናተር ስቴፋኒያ ክራክሲ የተመራ የጣሊያን የፓርላማ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።በውይይታቸውም፤ የሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል።በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ያሉ የተለያዩ የልማት እና የጸጥታ ችግሮችን በተመለከተም ሁለቱ ወገኖች ተወያይተዋል።የጣሊያን መንግስት ኢትዮጵያን በተለያዩ ዘርፎች ለመደገፍ የሚያደርገውን ትብብር አምባሳደር ታዬ አድንቀዋል።በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ሁለቱ ወገኖች ጠቁመዋል።አምባሳደር ታዬ ከሰብዓዊ ዕርዳታ በተጨማሪ በቀጠናው በልማት ፕሮጀክቶች ላይ በትብብር መስራት ለበርካታ ዜጎች ህይወት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አንስተዋል።በተጨማሪም ቀጠናዊ የጸጥታ ችግሮችን ከመቅረፍ አኳያ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር እና መግባባት አስፈላጊነት ላይ ምክክር መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
FBC
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ