ጆ ባይደን ድምጻቸው ደክሞ፣ በራስ መተማመናቸው ጠፍቶ፣ አቀርቅረው፣ ሃሳባቸው ተበትኖና አንደበታቸው ተሳስሮ ነበር ክርክሩን የጨረሱት።በክርክሩ ባይደን የትራምፕን የወንጀል ክሶች እና የ2020ውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመቀልበስ ያደረጓቸውን ሙከራዎች በማንሳት ሞግተዋል።የቀድሞው ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ባይደንን በኢኮኖሚ፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና በክርክሩ ባሳዩት ድክመት ሲተቿቸው አምሽተዋል።ለ90 ደቂቃዎች ከተካሄደው ክርክር በኋላ ከህዝብ የተሰበሰበ አስተያየት ትራምፕ 67 በመቶ ድምጽ በማግኘት ክርክሩን በሰፊ ልዩነት ማሸነፋቸውን አሳይቷል።
Al-Ain
More Stories
እየተጠናከረ የመጣው የብሪክስ ሀገራት ግንኙነት…
አሜሪካ ሶሪያን አጠቃች
የሩሲያ ጦር በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ ተፈጽሟል ላለው ጥቃት አፀፋ በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።