የኢፌዴሪ መከላከያ ጀኔራል መኮንኖች አዲስ አበባ ከሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር በዛሬው ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የአማራ ክልል የሰላም ኮንፈረንሰ ውይይት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተደርጓል፡፡
ወይይቱን የመሩት የክልሉ ተወላጅ የሆኑት የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ ÷ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል በላይ ስዩም ናቸው።
ተሳታፊዎችም አለ የሚሉትን ችግር በነፃነት በጥያቄም በሃሳብም የገለፁ ሲሆን ÷ ጥያቄያቸው ለክልል መንግስት እና ለፌደራል መንግስት ተደራጅቶ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
በጉባኤው ማጠቃለያው የመድረኩ ተሳታፊዎች ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫም አውጥተዋል መባሉን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …