አርቲስት ካሙዙ ካሳ እና ፋንታዬ ቱሪዝምና ትራቭል የኢትዮጵያን ቱሪዝምና የኤክስፖርት ዘርፉን ለማሳደግ የሚያስችሉ የቢዝነስ ስራዎችን በጋራ ለመስራት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ዱባይ ተፈራርመዋል፡፡
የስምምነቱ አላማ በፋንታዬ ግሩፕ ስር የሚገኘው ፋንታዬ ቱሪዝምና ትራቭል በኢትዮጵያ ቱሪዝም ዕድገት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የቱሪዝም ፓኬጆችን ከአርቲስቱ ጋር በመተባበር ለማቅረብ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የፋንታዬ ቱሪዝምና ትራቭል ካዘጋጃቸው የቱሪዝም ፓኬጆች ውስጥ፥ የኮንስትራክሽንና የኢንዱስትሪ ቱሪዝም፣ የግብርና ቱሪዝም፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቱሪዝም እና የደቡብ ኢትዮጵያ ባህላዊና ተፈጥሮአዊ ቱሪዝም ፓኬጆች ይገኙበታል።
እንዲሁም የምስራቅ ኢትዮጵያ አድቬንቸር የቱሪዝም እና የምዕራብ ኢትዮጵያ አስደናቂ የተፈጥሮ የቱሪዝም ፓኬጆች የተካተቱበት ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ የማይዳሰሱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ፌስቲቫሎችን በልዩ ሁኔታ አካቶ መቅረቡ ተገልጿል፡፡
በስምምነቱ የተካተቱት ፓኬጆች በኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው የፋንታዬ ቱሪዝምና ትራቭል ሥራ አስኪያጅ ዳዊት ዋለልኝ ገልፀዋል።
የአርቲስት ካሙዙ ካሳ ኩባንያ የሆነዉ ሻኩራ ፕሮዳክሽን እና ፋንታዬ ስቱዲዮ በጋራ በመተባበር የኢትዮጵያ የጥራጥሬና የቅባት እህል ምርቶች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪና ተመራጭ ሊያደርግ የሚያስችሉ የዶክመንተሪ ፊልሞችን በተለያዩ ቋንቋዎች ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ዶክመንተሪዎቹ በእንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ቻይንኛ፣ ጃፓኒኛ፣ ጀርመንኛ፣ ፐርሺያ፣ ሂንዱ፣ ኡርዱና እና በሌሎችም ቋንቋዎች ተዘጋጅተው በመላው ዓለም ተደራሽ እንደሚደረጉም ተጠቁሟል።
FBC
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።