የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ቢስት ባር” በሚዛን አማን ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ቢስት ባር” የተለያዩ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የብሔረሰቡ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በሚዛን አማን ከተማ መከበር ጀምሯል።”ቢስት ባር” የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ሲሆን ህዝቡ በሰላምና ጤና ወደ አዲስ ዘመን በመሻገሩ እና ከተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ተጠብቀው ለአዲስ ቀን በመድረሳቸው ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡበት ነው፡፡በብሔሩ አባላት ዘንድ በዓሉ ሲመጣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የይቅርታና የአብሮነት መንፈስ የተሞላበት ልዩ ዕለት በመሆኑ በድምቀት ያከብሩታል።በዓሉ በትላንትናው ዕለት የብሔሩ መነሻ ቦታ መሆኑን በሚነገርለት በሼይ ቤንች ወረዳ በምትገኘው ዣዥ ቀበሌ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችና የጎሳ መሪዎች በተገኙበት የተከበረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የበዓሉ ማጠቃለያ ዝግጅት በሚዛን አማን ከተማ በተለያዩ ስርአቶች በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ባማረ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው። ለበዓሉ ድምቀት የሚሆን የፖሊስ ማርቺንግ ባንድ የጎዳና ላይ ትርኢቱን አቅርቧል።ዘጋቢ ጦያር ይማም ከሚዛን ጣቢያችን
ደሬቴድ
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።