የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ መዲናዋ ቢሳው ተጉዟል።
23 ተጫዋቾችን ያካተተው ልዑካን ቡድኑ ከአዲስ አበባ በቶጎ (ሎሜ) አድርጎ ቢሳው ከተማ ዛሬ ምሽት ላይ እንደሚደርስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ወደ ጊኒ ቢሳው ከማምራቱ አስቀድሞ የመጨረሻ የሀገር ቤት ልምምዱን ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ማከናወኑ ተገልጿል።
FBC
More Stories
አንድሬ ኦናና ከቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ውጪ ሆነ
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ