በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር” የሚል ቃል አለ፤ ይህን መሰረት ብናደርግ እኛም እርስ በእርሳችን መነጋገራችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳየን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ፕሬዚዳንትፓስተር ጻዲቁ አብዶ ገለጹ።የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤በመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጥበበኞች ዘመኑን የሚያውቁ (የሚመክሩ) ‘ይሳኮር’ የሚባሉ ወገኖች እንደነበሩ ተናግረዋል።”ምክር በሰው ልብ እንደጠሊቅ ውኃ ነው፤አዕምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል”ይላል መፅሐፉ የሚሉት ፓስተር ጻዲቁ፤ ሀገራዊ ምክክሩ ሁሉንም የሚያካትት በመሆኑ ያላግባቡን ጉዳዮች ላይ በግልጽ መወያየት አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡”ኢትዮጵያውያን ለብዙ ሺህ ዘመናት በጎውንም ክፉውንም አይተናል ፤ አሁን ላይ ያሉ አለመግባባቶችን ሁሉ ወደ ጠረንጴዛ በማምጣት እና ሀገርን በማስቀደም ልንመክር ይገባል” ብለዋል፡፡
EBC
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።