የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የከተማ አስተዳደር (ክልላዊ) የምክክር ምዕራፉን በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፤ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በሚጀምረው በዚህ ምዕራፍ ላይ የሚከናወኑ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትን ይፋ አድርጓል።
በቀዳሚነት ለምክክሩ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች በምክክርና በውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን እንደሚያመጡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሂሩት ወልደስላሴ ተናግረዋል።
እነዚሁ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን የጋራ በማድረግ አሰባስበውና አደራጅተው የመፍትሔ ሀሳቦችን ያቀርባሉ ተብሏል።
በመጨረሻም የሂደቱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮቻቸውን እንደሚመርጡም ነው የተገለጸው።
በአዲስ አበባ ከተማ የተለዩ 2 ሺህ 500 የሚሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበትን ይህ የምክክር ምዕራፍ ለሠባት ቀናት የሚቆይ ነው።
FBC
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ