- ፅንስ በማህፀን ውስጥ እያለ ያለቅሳል፤ ፅንሱ ከሚለማመዳቸው ነገሮች ማለትም ከፊት እና ከአፍ እንቅስቃሴ ቀጥሎ አንዱ ማልቀስ ስለሆነ ነው፤ ሆኖም ግን የሽርት ውኃ ውስጥ ባሉ የቅባት እና የጡንቻ ፈሳሾች ምክንያት ድምፁን መስማት አይቻልም፡፡
- ፅንስ ከሰባተኛው ወር ጀምሮ ማሽተት የሚችል ሲሆን በተለይ መጥፎ ሽታን የመለየት አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡
- ከ18ኛው ሳምንት ጀምሮ ድምፅ መስማት የሚችሉ ሲሆን፤ ከተወለዱ በኋላ የእናታቸውን እና በተደጋጋሚ የሰሙትን ሰው ድምፅ በፍጥነት መለየት ይችላሉ፡፡
- ፅንስ በማህፀን ውስጥ በሚተኛበት ወቅት ህልም ሊያይ ይችላል፤ ህልሙም በማህፀን ውስጥ ስለሚያውቃቸው ነገሮች ነው፡፡
- ጨቅላ ህፃናት በተወለዱ ከ1 እስከ 2 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይፀዳዳሉ፤ ሆኖም ግን በማህፀን ውስጥ ሊፀዳዱም ይችላሉ፤ ይህም በተፈጥሮ እና የመውለጃ ግዜ በማለፍ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን የመፈጠር እድሉም እስከ 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡
- ቁመቷ 1.65 ሜትር እና ከዚያ በላይ የሆነች ሴት መንታ የመፀነስ እድሏ ከፍተኛ ነው፤ይህም ረዘም ያሉ ሴቶች ከጉበት የሚያገኙት የፕሮቲን መጠን ከፍ ያለ በመሆኑ የሚመረተውን ዕንቁላል መጠን ለመጨመር አስተዋፆ ስለሚያደርግ ነው፡፡
EBC
More Stories
ሕፃናት ወደ አፋቸው የሚያስገቧቸው ባዕድ ነገሮች እስከ ሞት ለሚያደርስ አደጋ እያጋለጣቸው ነው፦ የሕፃናት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት
የክልሉ ጤና ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት አመራሮች ያሳዩት አቋም ለህዝባቸው ያላቸውን ውግንና እና ለሙያቸው ያላቸውን ክብር ያረጋገጡበት ነው :- የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለፁ ።
በክልሉ ሁሉም ቀበሌዎች የተቀናጀ 2ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ በሽታ መከላከያ ክትባት ከግንቦት 22-25/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገለጸ።