
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያከናወናቸው የዲጂታል ሪፎርም ሥራዎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀልን የመከላከል አቅሙን ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዛሬ አመሻሹን የፌደራል ፖሊስ የዜጎች መረጃ መቀበያ ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የለማ እና ዜጎች ወንጀልን በቀላሉ ለማዕከሉ የሚጠቁሙበት EFPApp የተሰኘ መተግበሪያንም ስራ አስጀምረዋል።ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መከወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተው፤ በመንግሥታዊ ተቋማት ከ500 በላይ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መደረጋቸውን ጠቅሰዋል።ፌደራል ፖሊስም በማሻሻያው የዲጂታላይዜሽን አሠራርን በመተግበር ህብረተሰቡ በየትኛውም አካባቢ ሆኖ የወንጀል ድርጊትን መጠቆም የሚችልበትን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረጉ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት ተናግረዋል።ሁሉም ዜጋ መተግበሪያውን በመጠቀም ወንጀልን በጋራ የመከላከል ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል።
EBC
More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ