ሀገሪቱ ማዕቀቡን የጣለችው ለታይዋን የጦር መሳሪያ አቅርበዋል በሚል ነው
አሜሪካ ከሰሞኑ ለሩሲያ ድጋፍ አድርገዋል በሚል በቻይና ኩባንያዎች ላይ ተመሳሳይ ማዕቀብ ጥላለችቻይና በ12 የአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች።የዓለማችን ቁጥር አንድ እና ሁለት ልዕለ ሀያል ሀገራት አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ላይ ማዕቀብ እየጣሉ ይገኛሉ።ከሰሞኑ አሜሪካ በቻይና ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ለሩሲያ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ነው።ቻይናም 12 የአሜሪካ ጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ በመጣል በዋሽንግተን ለተደረገባት ቅጣት የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃለች።እንደ ሮይተርስ ዘገባ ቻይና ዋነኛ የአሜሪካ ጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያዎች ለታይዋን ድጋፍ አድርገዋል በሚል ማዕቀብ ጥላለች።ኩባንያዎቹ በተጣለባቸው ማዕቀብ ምክንያት በቻይና ያላቸው ሀብት እንዳይንቀሳቀስ፣ የኩባንያዎቹ አመራሮች ቻይናን እንዳይጎበኙ እና ከቻይናዊያን ጋር ግብይት እንዳይፈጽሙ ታግደዋል።በቻይና ማዕቀብ ከተቀጡ የአሜሪካ ጦር መሳሪያ እምራች ኩባንያዎች መካከል ሎክሂድ ማርቲን፣ ጀነራል ዳይናሚክስ እና ራይቲዮን ዋነኞቹ ናቸው።የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በዩክሬን ጦርነት ገለልተኛ መሆኑን በአንጻሩ አሜሪካ ግን ፍጹም ለዩክሬን እየደገፈች እንደሆነ ይህም ዘላቂ ሰላም እንደማያመጣ አስታውቋል።
Al-Ain
More Stories
የአውሮፓ ህብረት ያወጣቸውን ደንቦች መሠረት በማድረግ የግብርና ምርቶች ከደን ጭፍጨፋ ነፃ ሆነው እንዲመረቱ ከማድረግ አንፃር የግብርና ባለሙያዎች ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ ።
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡