የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ፎረም “ከፍተኛ ትምህርት ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ሀሳብ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል።ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ፎረም ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለማሻሻል የተለያዩ ተግባራት እየተከናኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል።ሚኒስትር ዴኤታው፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።የጥራት፣ የመልካም አስተዳደር እና የገንዘብ ድጋፍ ችግሮች ተቋማቱን እየፈተ ስለመሆኑ ነው የጠቆሙት።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለማሻሻል የሪፎርም ስራዎች እየተተገበረ መሆኑን ገልጸው፤የትምህርት ስርዓቱን ለመቀየር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።
EBC
More Stories
በዘንድሮ ዓመት በሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና አጠቃላይ ከሚፈተኑ 19ሺህ በላይ ተማሪዎች ዉስጥ ከ2ሺህ 6መቶ በላይ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተና እንደሚፈተኑ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ።
ከውሃ ሀብት የሚገኘውን ጥቅም ለማጎልበት መስራት ያስፈልጋል – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች