በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ መዳ ፉሪ ወረዳ በአንድ መጋዘን ውስጥ በህገወጥ መንገድ የተከማቸ ዘይት፣ ስኳር፣ ዱቄት፣ ሩዝ፣ ምስር እና የአፈር ማዳበሪያ ተያዘ፡፡
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ፉፋ መገርሳ እንደገለጹት÷ በቀረበ ጥቆማ መሠረት የፍርድ ቤት የፍተሻ ወረቀት በመያዝ በተደረገ ፍተሻ በዛሬው ዕለት ምግብ-ነክ ግብዓቶች እና የአፈር ማዳበሪያው ተይዟል፡፡
በዚህም 1 ሺህ ኩንታል ስኳር፣ 150 ኩንታል ሩዝ፣ 10 ኩንታል ምስር እና 700 ኩንታል የፍርኖ ዱቄት በመጋዘን ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ መገኘቱን ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም 560 ካርቶን ባለ 3 ሊትር እና 4 ሺህ ጄሪካን ባለ 20 ሊትር የምግብ ዘይትን ጨምሮ 250 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መያዙን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
FBC
More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ