

83ኛው የአርበኞች ቀን መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት በሚገኝበት ስፍራ ተከብሯል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ የአርበኞች ማህበር የበላይ ጠባቂ ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የጥንት አባቶቻችን በአርበኝነት ተጋድሎ ነፃነቷን አስከብረው ያቆዩልንን ሃገር እና ነፃነት አፅንተን ማቆየት የሁላችንም ሃላፊነት ነው ብለዋል፡፡ ትላንት አባቶቻችን ለኢትዮጵያ ነፃነት ህይወታቸውን መስዋዕት ከፍለውልናል ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ አሁን ያለነው ትውልድ ደግሞ የጋራ ጠላታችን የሆነውን ድህነትን በተባበረ ክንዳችን ድል ነስተን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ በትጋት መስራት አለብን ሲሉ ገልፀዋል። በክብረ በዓሉ ላይ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊትን በመወከል የተገኙት የመከላከያ የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል ሀጫሉ ሸለመ፤ አርበኝነት በትውልድ ቅብብሎሽ የሚቀጥል የኢትዮጵያዊያን መገለጫ እሴት ነው ብለዋል፡፡
EBC
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።