
በባሕር ዳር ከተማ በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባው አዲሱ የዓባይ ድልድይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የዓባይ ድልድይ በኢትዮጵያ ከተሰሩ የድልድይ ፕሮጀክቶች በስፋቱም በርዝመቱም ግዙፍ ፕሮጀከት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደመንግስት ሁለት ድልድይ ለመገንባት እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመጀመሪያው ልማትን የሚያሳልጥ ድልድይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ህዝብን የሚለያይ ግድግዳ በማፍረስ የአንድነት ድልድይ መገንባት ነው ብለዋል፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል። አዲሱ የዓባይ ድልድይ 380 ሜትር ርዝማኔ ያለው ሲሆን፤ 43 ሜትር የጎን ስፋት እንዳለውም ተጠቁሟል።
FBC
More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ