የሩሲያ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ሳቢያ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የሚታየውን የዋጋ መለዋወጥ ለመቋቋም ከመጋቢት 23 ቀን 2018 ጀምሮ የቤንዚን የውጭ ኤክስፖርት ለማገድ መወሰኑ ታውቋል።
የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ የኢነርጂ ሚኒስቴር እገዳውን የሚጥል ረቂቅ ውሳኔ እንዲያዘጋጅ ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆን እገዳው እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ድረስ እንደሚቆይ የሩሲያ መንግስታዊ የዜና ወኪል ታስ ዘግቧል።
ሩሲያ ይህን እርምጃ የወሰደችው የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋጋትና የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ነው ተብሏል።
ሩሲያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ ቤንዚን ወደ ውጭ ሀገራት ልካለች። አሁን የተጣለው እገዳ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የራሱ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይገመታል።
መረጃው የ’ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ’ ነው።
More Stories
ኢራን በእስራኤል የኢንዱስትሪ ማዕከል ላይ የሚሳዔል ጥቃት ፈጸመች
ኢራን የፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ 20 ተጨማሪ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲያልፉ ፈቀደች
የሁቲ ሁለተኛ ዙር ጥቃት እና የአሜሪካ እግረኛ ጦር…