March 27, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ትራምፕ በኢራን ላይ እንፈጽማለን ላሉት ጥቃት ያስቀመጡትን ቀነ ገደብ በድጋሚ አራዘሙ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ካልከፈተች በኃይል መሰረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያስቀመጡትን ቀነ ገደብ በድጋሚ አራዘሙ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከሳምንት በፊት ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በ48 ሰዓታት ውስጥ ክፍት እንድታደርግ አሳስበው፥ ይህን የማታደርግ ከሆነ በኃይል መሰረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ከኢራን ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፥ ያስቀመጡትን ቀነ ገደብ ወደ አምስት ቀናት ማራዘማቸው አይዘነጋም፡፡

ኢራን በበኩሏ ከአሜሪካ ጋር የጀመረችው ድርድር እንደሌለ መግለጿ የሚታወስ ሲሆን፥ ፕሬዚዳንቱ ለቴህራን የሰጡትን ቀነ ገደብ ለተጨማሪ 10 ቀናት ማራዘማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከሳምንት በፊት ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በ48 ሰዓታት ውስጥ ክፍት እንድታደርግ አሳስበው፥ ይህን የማታደርግ ከሆነ በኃይል መሰረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ከኢራን ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፥ ያስቀመጡትን ቀነ ገደብ ወደ አምስት ቀናት ማራዘማቸው አይዘነጋም፡፡

ኢራን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በላከችው ደብዳቤ፥ ጦርነት አወጁብኝ ካለቻቸው ሀገራትና አጋሮቻቸው ውጪ ያሉ መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲያልፉ መፍቀዷን አስታውቃለች፡፡