March 26, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በቦንጋ ከተማ ተከፈተ

ደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በቦንጋ ከተማ ተ

ፕሮግራሙን አስመልክቶ የድርጅቱ ሥራ-አስኪያጅ አቶ ዘላለም ገነሞ ለድርጅቱ አድማጭ ተመልካቾች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በ50 የብሄር ብሄረሰቦች ቋንቋዎች የሚሰራና በአፍሪካ ደረጃ ተሞክሮ የሚወሰድበት ማዕከል መሆኑን አቶ ዘላለም ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ ፍትሃዊ የሚዲያ አገልግሎት ለ4ቱም ክልሎች እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሕዝቦችና ከመንግስት ፍላጎት ጋር አብሮ የሚሄድና ዘላቂ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በዕቅድ ከተያዙት ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ቋሚ የጽህፈት ቤቱ መክፈት ሲሆን የሁሉም ቅንጅትና ትብብር ታክሎበት የክልሉ ማስተባበሪያ ስቱዲዮ በቦንጋ ሥራ መጀመሩን አብስረዋል፡፡

የስቱድዮው መቋቋም ዋናው ጉዳይ መንግስትና ሕዝቦች ፍትሃዊ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ መስራት መሆኑን የገለጹት አቶ ዘላለም ከዚህ ቀደም ከርቀት አኳያ ይከሰት የነበረውን እንግልት ለማስቀረት የሚያስችል መፍትሄ እንደሆም አስረድተዋል፡፡

የክልሉ አስተዳደርና ፖለቲካ መቀመጫ በሆነችው ቦንጋ ከተማ ላይ ማስተባበሪያ ጣቢያ መቋቋሙ የሚዲያ አገልግሎቶች በቅርበት ተደራሽ ለማድረግ የታቀደ መሆኑን ነው አቶ ዘላለም የገለጹት፡፡

ስቱዲዮው እንዲሳካ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ያደረጉት ድጋፍ ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቶ ዘላለም አቅርበዋል፡፡

አቶ ዘላለም አያይዘው ጅምር ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ተቋሙ የታለመለትን ግብ ማሳካት እንዲችል አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል።

የይዘት ሥራዎች በጥራት በመጠንና ፈጠራ ታክሎበት መሠራት እንዳለበት ገልፀው አሁን ላይ የዜና ሽፋን ሥራዎች የተጀመሩ መሆናቸውንና ተጨማሪ ተግባራት እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ለማስተባበሪያው የይዘት ሥራዎችን የማቅረብ ተግባራት በዋናነት ከ4ቱም ቅርንጫፍ ጣቢያዎች እንደሚጠበቅ ጠቅሰው ዋና ጣቢያውም የይዘት ሥራዎች ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ በኤዲቶሪያል ፖሊሲ መሠረት የመፈተሽና የማስተካከል ሚናውን እንደሚወጣ መናገራቸውን ቦንጋ ኤፍ ኤም ዘግቧል።