በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኳታር ተወካይ ሂንድ ቢንት አብዱልርሃማን አል ሙፍታህ የኢራን ጥቃቶች የኳታርን የግዛት አንድነት እና የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን የጣሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ተወካዩዋ በንግግራቸው “የኢራን ከባድ መዘዝ የሚያስከትሉ ጥቃቶች በዓለም ላይ ያለውን ሰላም እና ደህንነት ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ መብቶችንም እየጎዱ ነው” በማለት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶችን አውግዘዋል።
አክለውም “እነዚህ ጥቃቶች ለኛ ትልቅ የጭንቀት ምንጭ ናቸው ስለዚህ ከእንግዲህ ዝም ማለት አንችልም” ሲሉ ተደምጠዋል።
የኳታሯ ተወካይ በተጨማሪም የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት “በኢኮኖሚው እና በአቅርቦት መስመሮች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አስከፊ መዘዝ ከግምት ውስጥ በማስገባት” ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
ኳታር በኢራን ጥቃቶች 17 በመቶ የሚሆነውን የተፈጥሮ ጋዝ ለዓለም ገበያ የማቅረብ አቅሟን እና 20 ቢሊየን ዶላር አመታዊ ገቢዋን እንደምታጣ መገለጿ ይታወሳል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
More Stories
በ48 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ወጪ 500 ሺህ ዘመናዊ ቆጣሪዎችን ለመግጠም እየተሰራ ነው
የእናቶችንና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በመስክ ምልከታው የተገኘው ልምድ የሌማት ትሩፋት አካል በመሆኑ አርሶ አደሮቻችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል፦