እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ኢስፋሃን እና ኮራምሻህር የኢነርጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የኢነርጂ መሰረተ ልማት ላይ ለመፈፀም የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ወደ አምስት ቀናት መራዘሙን ትናንትና ካስታወቁ በኋላ ጥቃቱ መፈጸሙን ዘገባዎች አመልክተዋል።
የኢራን መገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ አናዶሉ እንደዘገበው፤ በኢስፋሃን የኢነርጂ ጣቢያ በተፈፀመው ጥቃት በአካባቢው የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ አስተዳደር ህንጻ እና የጋዝ ግፊት መቆጣጠሪያ ማዕከል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
በተመሳሳይ በኮራምሻህር የኢነርጂ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመ ጥቃት በጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ በሁለቱም የኢነርጂ መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈፀመው ጥቃት የከፋ ጉዳት አለመድረሱ እና በሁለቱም ስፍራዎች ያለው የኃይል አቅርቦት እንዳልተስተጓጎለ ነው የተገለጸው፡፡
ከጥቃቱ በኋላ ኢራን በወሰደችው አጸፋ በእስራኤል ኔጌቭ፣ ዲሞና፣ ቴል አቪቭ እና ኤሊያት ከተሞች እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን አብዮታዊ ዘብ አስታውቋል፡፡
ምሽት ላይ ኢራን በቴል አቪቭ በፈጸመችው ጥቃት በመኖሪያ ህንፃዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስ፤ ስድስት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ማስተናገዳቸውን የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
More Stories
አሜሪካና ኢራን ንግግርን በተመለከተ ያንጸባረቁት ተቃራኒ ሃሳብና የነዳጅ ዋጋ ዳግም መናር …
ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል ለመወሠን የሚያስችለውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀመረ
በኢራን ጉዳይ ቻይና ጥሪ አቀረበች