የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈጣን ዕድገቱና በስፋቱ የሚታወቀውን የቻይና የቡና አምራችና አቅራቢ ድርጅት ኮቲ ኮፊ (Cotti Coffee) አመራሮች ጋር በክልሉ በቡና ዘርፍ ለመሰማራት ባለው እቅድ ዙሪያ ተወያዩ።
የቻይና የቡና አምራችና አቅራቢ ድርጅት ኮቲ ኮፊ (Cotti Coffee) በዓለም ዙሪያ በ33 አገራት ውስጥ ከ20,000 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ በቅርንጫፍ ብዛት በዓለም አቀፍ 3ኛውን ደረጃ የያዘ ግዙፍ የቡና ኩባንያ ነው።
ኩባንያው ቅርንጫፉን ይበልጥ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የራሱን የቡና ልማት ለመጀመር ዕቅድ መያዙን ገልጿል።
በዚህም ጥሬ ቡናን ቆልቶና አቀነባብሮ ለዓለም ገበያ የሚያቀርብበት ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመገንባት ማቀዱንም ለክልሉ መንግስት በማሳወቅ ለዚህም አስፈላጊ ትብብርና ድጋፍ እንዲደረግም ጠይቋል።
በውይይቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ከቻይና ቡና አምራችና አቅራቢ የኢንቨስትመንት ጥያቄ አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
ኩባንያው በአካባቢው ለሚያከናውነው የቡና ልማትና የእሴት ጭማሪ ስራ የሚሆን መሬት ለማቅረብ ክልሉ ዝግጁ እንደሆነ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያብራሩት።
የቡና ኢንቨስትመንቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድል ከመፍጠሩም ባለፈ፣ ክልሉ ቡናን በጥራትና እሴት ጨምሮበት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝም ገልጸዋል።
ይህም የቻይና ቡና አምራችና አቅራቢ ድርጅት ኮቲ ኮፊ (Cotti Coffee) እና በክልሉ መንግሥት መካከል የተጀመረው ትስስር፣ የክልሉን የቡና ዘርፍ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይታመናል ሲል የዘገበው የክልሉ
More Stories
ሚኒስቴሩ ለሦስት ኩባንያዎች የማዕድን ምርት ፍቃድ ሰጠ
በክልሉ ከሚገኙ ቡና አቅራቢ ነጋዴዎች ጋር በወቅታዊ የቡና ገበያ ላይ በቦንጋ ከተማ ምክክር እየተደረገ ነዉ
የጣሊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያጠናከሩ ተጠየቀ፡፡