ማሻ፤ መጋቢት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የ31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይጀመራል፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ከሜዳው ውጪ ከቦርንማውዝ ይጫወታል፡፡ ቦርንማውዝ ከማንችስተር ዩናይትድ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም፡፡
ማንችስተር ዩናይትድ ማይክል ካሪክን ጊዜያዊ አሰልጣኘ አድርጎ ከሾመ በኋላ 22 ነጥቦችን በመሰብሰብ ቀዳሚው ሲሆን ዛሬም ለሌላ ሦስት ነጥብ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
በቪታሊቲ ስታዲየም በሚደረገው ጨዋታ ጀስቲን ክላይቨርት፣ ሉዊስ ኮክ፣ ቴይለር አዳምስ እና ጁሊዮ ሶለር ከባለ ሜዳዎቹ በኩል በጉዳት የመሰለፋቸው ነገር አልተረጋገጠም፡፡
በዩናይትድ በኩል ፓትሪክ ዶርጉ፣ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ማቲያስ ዴሌክት አሁንም በጉዳት ቡድኑን የማያገለግሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ ዩናይትድ ዛሬ ጨዋታውን ካሸነፈ ከማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት የሚያጠብ ይሆናል፡፡
More Stories
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነቷ እንዲሰረዝ መወሰኑ አሳፋሪ ነው፡- የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኦጉስቲን ሴንግሆር
31ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ነገ ጀምሮ ይካሄዳሉ!
ማንቼስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ…