March 17, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የእስያ አገራት ነዳጅ ለመቆጠብ የሥራ ቀናትን ከመቀነስ አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው

ማሻ፤ መጋቢት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) እስያዊቷ አገር ሲሪ ላንካ፤ በኢራን ጦርነት ምክንያት ሊፈጠር የሚችል የነዳጅ እጥረትን ለመቋቋም በየሳምንቱ ረቡዕ ዕለት እንደ የሕዝብ በዓል ተቆጥሮ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ ወሰነች።

ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችም ምን ያህል ነዳጅ መግዛት እንደሚችሉ የሚወስን የራሽን ካርድ እንዲይዙ ተደርጓል።

የሲሪ ላንካ ፕሬዝዳንት አኑራ ኩማራ ዲሳናያኬ ሰኞ ዕለት በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ “ለከፋው ነገር መዘጋጀት አለብን፤ ነገር ግን ጥሩ ነገር እንደሚመጣ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

ሲሪ ላንካ ይህንን እርምጃ የወሰደችው በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠር በርሜል ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋቱን ተከትሎ ሌሎች የእስያ አገራት የቁጠባ ውሳኔዎችን ካሳለፉ በኋላ ነው።

ባለፈው ዓመት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ካለፈው ነዳጅ እና ጋዝ ውስጥ 90 በመቶ የሚጠጋው የደረሰው ወደ እስያ ነው።

ሌሎችም የእስያ አገራት በጦርነቱ ምክንያት የነዳጅ እጥረት እንዳይፈጠር በመስጋት እርምጃዎችን ወስደዋል።

ምያንማር – የግል ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቀድላቸው አንድ ቀን እያለፉ ነው። በየትኛው ቀን የቱ ተሽከርካሪ ይንቀሳቀሳል የሚለው የሚወሰነው በሰሌዳ ቁጥር ነው።