March 17, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ የሀገራትን ዕጣ ፈንታ በሚወስነው የዲጂታል ዘመን ደጃፍ ላይ ትገኛለች

ማሻ፤ መጋቢት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8)፦ ኢትዮጵያ የሀገራትን ዕጣ ፈንታ በሚወስነው የዲጂታል ዘመን ደጃፍ ላይ ትገኛለች ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የትውልድ ርዕይ! በሚል ርዕስ ባወጣው መልዕክት ኢትዮጵያ የሀገራትን ዕጣ ፈንታ በሚወስነው የዲጂታል ዘመን ደጃፍ ላይ ትገኛለች ብሏል።

የኢትዮጵያ ዲጂታል 2030 ብሔራዊ ምላሻችን፤ በራስ በመተማመን፣ በፈጠራ እና በታላቅ ዓላማ ተንቀሳቅሰን ያሳየነው ቁርጠኝነትና የማድረግ አቅም ነው ሲልም አስታውቋል።