March 15, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሴዑል ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸነፉ

ማሻ፤ መጋቢት 6/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የሴዑል ማራቶን በወንዶች አትሌት ሀፍቱ ተክሉ በሴቶች አትሌት ሔቨን ኃይሉ አሸንፈዋል።

በወንዶች ውድድር አትሌት ሀፍቱ ተክሉ በ4 ዓመት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን÷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:04:23 ወስዶበታል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጌታነህ ሞላ 2:04:25 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ÷ አትሌት ፀጋዬ ታደሰ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል።

በሴቶቹ ውድድር ደግሞ አትሌት ሔቨን ኃይሉ 2:19:10 በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባ አሸንፋለች።

አትሌት በቀለች ጉደታ 2:19:40 በመግባት በውድድሩ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ÷ አትሌት ቦሰና ሙላቴ 2:19:48 በመግባት ሦስተኛ እንደወጣች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።