March 10, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጦርነቱ በምን ሊቆም ይችላል ? የኢራን ስልታዊ እጅ መጠምዘዣ ጦርንት!

ኢራን ከአሜሪካ ጋር “ ለረጅም ጊዜ ጦርነት ነው የተዘጋጀሁት  ፤ ለዲፕሎማሲ የሚሆን ቦታ የለኝም “ አለች።

በአሜሪካ/እስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ጦርነት 10ኛ ቀኑን በያዘበት በአሁኑ ወቅት ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ረጅም ጦርነት መዘጋጀቷንና ለዲፕሎማሲ ቦታ እንደሌለ ገልጻለች።

የኢራን ጠቅላይ መሪ የውጭ ጉዳይ አማካሪው ካማል ካራዚ ለሲኤንኤን በሰጡት ቃል “ ዶናልድ ትራምፕ ሌሎችን ሲያታልል የቆየና የገባውን ቃል የማይጠብቅ ሰው ነው፤ ይህንንም በሁለት ዙር ድርድሮች ወቅት በተግባር አይተነዋል፤ ከእንግዲህ ለዲፕሎማሲ ቦታ የለም “ ብለዋል።

ይህ ጦርነት ሊቆም የሚችለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጠረው ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጫና በተለይም የነዳጅ ዋጋ መናር ሌሎች አገራት ጣልቃ ገብተው አሜሪካን እንዲያስቆሙ ሲያስገድዳቸው ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

በጦርነቱ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል ከ100 ዶላር በላይ ዘሏል፤ የዓለም የነዳጅ አቅርቦትም 20 በመቶ መስተጓጎሉ ተነግሯል።

የሟቹ ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ ልጅ የሆኑት ሞጅታባ ካሜኒ የአገሪቱ ከፍተኛ መሪ ሆነው መሾማቸው ኢራን ለጦርነቱ ያላትን ቁርጠኝነትና ቀጣይነት እንደሚያሳይ ተመላክቷል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶላንድ ትራምፕ የካሜኒ ልጅ ሹመት አላስደሰታቸውም።

የኢራን ጠቅላይ መሪ የውጭ ጉዳይ አማካሪ ካማል ካራዚ “ ይህ የእሱ ስራ አይደለም “ በማለት ውድቅ አድርገውታል። አዲሱ መሪ የአገሪቱን የመከላከል አቅም የመምራት ኃላፊነት እንዳለባቸውም አክለዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢራን 60 በመቶ የሚሆነውን የተኩስ አቅሟን በመጠቀም በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችንና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን ኢላማ እያደረገች መሆኑን የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) አስታውቋል።

መረጃው የሲኤንኤን ነው።