የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአመራር ግምገማና ምዘናው ከብልፅግና ፓርቲ ዕሳቤና መርሆዎች መነሻ ተቋማት የተጣለባቸውን የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአመራር መሪነት የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር የሚገመግም እንደኾነ በመድረኩ ተገልጿል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በመድረኩ መክፈቻ ወቅት እንደገለጹት፥ የአመራር ምዘናው ጠንካራ ተቋም በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው።
አመራሩ የብልፅግና ፓርቲ ተልዕኮዎችን በብቃት በመፈጸም የህዝብ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በዚህም ረገድ ባለፋት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ይገመግማል ብለዋል።
ምዘናው የመልካም አስተዳደር እና የህዝብ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በአመራሩ መሪነት የተከናወኑ ተግባራትን የሚፈትሽ እንደኾነም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
አመራሩ ሁሉን-አቀፍ አሰተሳሰብ በማንገብ በየደረጃው ችግር ፈቺ ድጋፍና ክትትል በማድረግ መልካም ተሞክሮዎችን የማስቀጠል እንዲሁም ማነቆዎችን ከመፍታት አኳያ የተከናወኑ ተግባራትም በዝርዝር ይገመግማል ብለዋል ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ።
የምዝናውን ዓላማና አስፈላጊነት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው፤ የአመራር አፈጻጸም ምዘና ውጤትን መሰረት ያደረገ፤ ግልጽ፣ ወጥና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በማስፈጸም የፓርቲውን አመራር ጥራትና ውጤታማነት ማሳደግ ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ ነው ብለዋል።
ምዘናው ጠንካራ የአመራር አሀድ በመፈጠር የመንግሥትና የፓርቲ ኢንሼቲቮችንና መደበኛ ተግባራትን በተሻለ መልኩ በመፈጸም ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚረዳ እንደኾነም አቶ ፍቅሬ ገልጸዋል።
“አመራሩ ተግባራትን በጊዜ የለኝም ስሜት መፈጸም አለበት” ያሉት አቶ ፍቅሬ፥ በዝግጅት ምዕራፍ በአመራሩ መካከል ተነሳሽነት፣ ከአንድ በላይ ተግባራት በአንድ ጊዜ አቀናጅተው መፈጸም የሚችል አመራር መፈጠሩን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ በተግባር ምዕራፍ ከአስተሳሰብና የተግባር ውጤታማነት አኳያ ውስንነቶች መስተዋላቸውን በመጠቆም ግምገማ እነዚህ ብልሽቶችን በማረም ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ ነው ብለዋል።
ዘገባው የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።
More Stories
በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
በሸካ ዞን የፍትህ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ሚና ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገለጸ
መንግስት በዜጋ ተኮር ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አያሌ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።