የከተማ ውበትና ዕድገት ማምጣት እንዲቻል ህብረተሰቡ ከተማውን በባለቤትነት መንከባከብ እንደሚገባው የማሻ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ።
ለምክር ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በአቶ አንዱዓለም ጌታቸው ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርት መነሻነትም የምክር ቤቱ አባላት አስተያየታቸውን ሰተዋል።
በማህበራዊ፣ኢኮኖናዊና የመልካም አስተዳደር የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ለአብነትም በጤናው ዘርፍ በከተማው የህብረተሰብ መድሀኒት መደብር ባለመኖሩ ህዝቡ እየተስተጓጐለ በመሆኑ ያሉትን ችግሮች መፍታት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የማዘጋጃ ቤት ገቢ ለከተማ ለውጥ የጀርባ አጥንት ቢሆንም እንደ ማሻ ከተማ ማዘጋጃ መስተካከል ያለበትን ችግር በመፍታት በቀጣይ ትኩረት ተሰቶት መስራት ያስፈልጋል ተብሏል።
በከተማው ውስጥ የመንግስት ተቋማት ግንባታ ስራ በጊዜ ያለመጠናቅና የከተማ ኮሪደር ስራ ጉዳይ መንግስት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ችግሮቹን በመለየት በህግ አግባብ መመራት እንዳለበት የምክር ቤት አባላቱ ጠይቀዋል።
በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጣራ በኩል የተሰራ
ስራ በቂ ባለመሆኑ የሥራ ፈላጊ ወጣት ቁጥር በበዛ ቁጥር ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ አስፈላጊውን ስራ መስራት እንደ ከተማ የትኩረት አቅጣጫ መሆን እንዳለበት ተነስቷል።
ምክር ቤቱ የህዝብ ድምፅ በመሆናቸው የከተማ እድገትና ሠላም ለማስጠበቅ አስፈፃሚ አካላት እስከ ህብረተሰብ በመውረድ የአንበሳውን ድርሻ መወጣት ይጠበቃል ሲሉ አንስተዋል።
በከተማ ውስጥ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሁሉም ተሳትፎ የተሻለ መሆኑን የገለፁት የምክር ቤት አባላቱ ቀጣይነት እንዲኖረው አሳስበዋል።
ገቢ የከተማ ውበት ለውጥና እድገት ያለው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ በዘርፉ የተሰራ ስራ የተሻለውን በማስቀጠል ቀሪዎቹን ስራ የእኔ ነው በሚል ስሜት መፈፀም ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ለተነሱ ጥያቄዎች የከተማ ከንቲባ በአቶ አንዱዓለም ጌታቸውና በየዘርፉ ኃላፊዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት አቅጣጫ ተቀምጦ ጉባኤው ተጠናቋል።
ዘጋቢ: ኢያሱ ሸግቶ
More Stories
በሸካ ዞን የፍትህ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ሚና ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገለጸ
የአመራር ምዘናው ጠንካራ ተቋም በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው -ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
መንግስት በዜጋ ተኮር ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አያሌ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።