ዜጋ ተኮር ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶች ተፈፃሚ ከሚሆንባቸው መንገዶች አንዱ የበጎነት ተግባር ሲሆን በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ከማድረግም ባለፈ ለዜጎች የተሻለ የኑሮ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ ይገኛል።
በዚህም የፌዴራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አቅም ደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እጅግ ዘመናዊ ቤቶችን ለመገንባት የዛሬ ሁለት አመት ነሐሴ ወር ውስጥ ነበር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ያካሄደው።
በወቅቱ ከኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጋር ፕሮጀክቱን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ቤቶቹ ተጠናቀው ለአቅመ ደካማ ዜጎችን ተጠቃሚ እንዲደርግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
እነዚህ ቤቶች በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዛሬ ከማስጀመሪያነት ባለፈ እጅግ ባማረ ሁኔታ ተጠናቀውና በሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ በወ/ሮ ሁሪያ አሊ ተመርቀው ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላልፈዋል።
ቤቶቹ የተለያዩ ክፍል ያሉት መኖሪያ ክፍል ፣መፀዳጃ ክፍል ፣ የሶላር ኃይል አገልግሎት፣ የቆሻሻ ማስወገጃ ሥርዓት እና የውሃ ማጠራቀሚያ አማራጭ ያለው መሆኑ ልዩ ያደርጋል።
እነዚህ ቤቶችጰመንግስት አካታች ማህበራዊ ልማት ለማረጋገጥና ለዘጎች ምቹ የኑሮ ሁኔታ ለማመቻችት እያደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ ጥረት ማሳያ እንደሆኑም ታውቋል።
ይህ ፕሮጀክት መጠለያ ቤት ብቻ ሳይሆን መንግስት ለዜጎች ክብር የሚሰጠውን ትልቅ ቦታ በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነም ተገልጧል።
ትላንት ዕቅድ የነበረውና ዛሬ ወደ ተግባር የተቀየሩ እነዚህ ውብና ዘመናዊ አምስት የመኖሪያ ቤቶች 3 አባዎራዎችና 2 እማወራዎች በአጠቃላይ 20 የቤተሰብ አባላት በፍቅር የሚኖሩበት ምቹ መጠለያ ሆኗል።
በእነዚህ ቤቶች ምክንያት የ20 አቅመ ደካማ ዜጎች እምባ ታብሷል፣ ህፃናት በምቹ መኖሪያ ቤት ሆነው ነገን በብሩህ ተስፋ እንዲኖሩና እንዲማሩም አስችሏል።
More Stories
በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
በሸካ ዞን የፍትህ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ሚና ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገለጸ
የአመራር ምዘናው ጠንካራ ተቋም በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው -ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)