ማሻ፤ የካቲት 23/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ የዓድዋ ድል በአፍሪካ ታሪክ አንዲት ሀገር በቅኝ ገዥ ኃይል ላይ የተቀዳጀችው የመጀመሪያው ድል በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጽዕኖ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ድሉ የኢትዮጵያውያንን የጽናት መንፈስ ከማረጋገጡ ባለፈ በመላው አፍሪካ ለሚካሄዱ የነፃነት ትግሎች መነሻ መሆኑንም አክለዋል።
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ የወዳጅነት ታሪክ እንዳላቸው የጠቀሱት ሰርጌይ ላቭሮቭ፤ በየተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ፍትሃዊ የዓለም ሥርዓት እንዲኖር በጋራ እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ እና በባህል ዘርፎች ትብብሮች እያደጉ መሆናቸውን መግለጻቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታን ጨምሮ፣ የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልን መልሶ መገንባት እና የጋራ ባዮሎጂካል ምርምር ማዕከል መመሥረት ዋና ዋናዎቹ የትብብር ፕሮጀክቶች ስለመሆናቸው ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው መጥቀሳቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
More Stories
ትውልዱ የዓድዋን የድል መንፈስ በመላበስ የሀገሩን ሰላምና ዕድገት የማረጋገጥ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት፦ አርበኞችና ስካውቶች
የባሕር በር የማግኘት መብታችን የዓድዋ ሰማዕታት ካወረሱን የሉዓላዊነት አደራ የማይነጠል ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ማሻ ቅርንጫፍ ሰራተኞች የአድዋን ድል በዓል፣ ዋናው ጣቢያ የተመሰረተበን 21ኛ ዓመት እና ቅርንጫፉ ስርጭት የጀመረበትን 2ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።