February 25, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

ማሻ፤ የካቲት 17/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ለእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን አስጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ለሀገር ሉዓላዊነትና ለነፃነት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች ታሪክ ለፕሬዚዳንቱ ተብራርቶላቸዋል።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባተላለፉት መልዕክት፤ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለነበራቸው ቆይታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማና ስኬታማ እንዲሆን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነም ታምኖበታል።